10ቱ ለውትድርና የተዘጋጀ የሰው ኅይል ያላቸው አገራት

0
634

የሕዝብ ብዛት ለአንዳንድ አገራት ሀብት ለአንዳንዶች ደግሞ ከባድ ፈተና ሆኖ ይታያል። ታድያ ዓለም ሁሉ ሊስማማ በሚችልበት ደረጃ ደግሞ የሕዝብ ብዛት ለውትድርና የሰው ኀይል በብዛት ለማፍራት ጠቃሚ ሆኖ ይገኛል። ይህንን መሠረት አድርጎ፣ ኢንዴክስሙንዲ የተባለ የመረጃ አውታር፣ ከሲአይኤ ወርልድ ፋክት ቡክ አግኝቼ ነው ብሎ ያስነበበው መረጃ እንደሚያሳየው፣ አገራት እንደ ሕዝብ ብዛታቸው ሁሉ ለውትድርና ሊያቀርቡ የሚችሏቸው ብዙ ዜጎች አሏቸው።

በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር እስከ 2010 ድረስ በተሰበሰበና እስከ 2018 ድረስ ትክክለኛነቱ ተረጋግጦ በቆየ መረጃ መሠረት፤ ቻይና በዓለማችን ላይ ለውትድርና ዝግጁ ሊሆን የሚችል ብዙ ዜጋ ያላት አገር ሆና ተመዝግባለች። ይህ ሲተነተን፣ በቻይና በኩል ምንም ዓይነት ጦርነት ቢነሳ እንኳን፣ ውትድርናውን መቀላቀል በሚችልበት አቋም ላይ የሚገኝ ብዙ ዜጋ አላት ማለት ነው፤ ቻይና።

ይህ ነገር አንድም የሕዝብ ብዛት ውጤት ሳይሆን አልቀረም። በኹለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው አገር ሕንድ መሆኗም ይህን ያሳብቃል። ከዛ በተረፈ አሜሪካ፣ ኢንዶኔዥያ ብራዚል እያለ ዝርዝሩ እየወረደ ሲሔድ ከመጀመሪያዎቹ ቻይና እና ሕንድ አንጻር ቁጥሩ ከእጥፍ በላይ እንደሚያንስ ለማየት ይቻላል። እንደ ሞናኮ ያሉ አገራት ደግሞ በአንጻሩ ለውትድርና ሰው አበርክቱ ቢባሉ ከ3 ሺሕ ያነሰ የሰው ኀይል ብቻ የሚያቀርቡ ናቸው።

ናይጄሪያ እንደ ሕዝብ ብዛቷ ሁሉ በዚህም ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆና ተገኝታለች። በ21‚012‚200 ለውትድርና በሚሆን የሰው ኀይል የምትከተለው ግብጽ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ኢትዮጵያም ግብጽን በመከተል በዓለም 17ኛ በአፍሪካ ደግሞ 3ኛ ሆና 19‚067‚500 ያህል ብዛት ያለው የሰው ኀይል ለውትድርና በሚበቃ አቋምና ሁኔታ ላይ የሚገኝባት አፍሪካዊት አገር ተብላ በዝርዝሩ ተቀምጣለች።

ቅጽ 1 ቁጥር 50 ጥቅምት 8 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here