መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናበፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ የሆኑ ሠራተኞች በጡረታ ዐቅድ እንደሚካተቱ ተገለጸ

በፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ የሆኑ ሠራተኞች በጡረታ ዐቅድ እንደሚካተቱ ተገለጸ

ከመስከረም 1 ቀን 2015 ጀምሮ በፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ የሆኑ ሠራተኞችን ወደ ጡረታ ዐቅድ የማካተት አሰራር በኹሉም የግል ድርጅቶች ተግባራዊ እንደሚደረግ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አስታውቋል።

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ገመቹ ዋዩማ በሰጡት መግለጫ፤ ከመጋቢት ወር 2014 ጀምሮ ተቋሙ የአዋጅ ማሻሻያ በማድረግ ወደ ሥራ መግባቱን ተናግረዋል።

በፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ የነበሩ ሠራተኞችን በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ ዕቅድ ስለሚሸፈኑበት ኹኔታ መመሪያ ማውጣት ከአዋጁ ማሻሻያ ውስጥ አንዱና መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑንም አስረድተዋል።

መመሪያው በግል ድርጅት ሠራተኞች ዕቅድ ያልተሸፈኑ ሠራተኞች በጡረታ ዕቅድ የሚሸፈኑበት እና የተጠራቀመ የፕሮቪደንት ፈንድ ገንዘብ ለጡረታ ፈንድ ገቢ በማድረግ፤ ቀደም ሲል የፈጸሙት አገልግሎት ለጡረታ አበል አወሳሰን እንዲታሰብ እንደሚያስችልም ተናግረዋል።

መመሪያው ከ2003 በፊት በተቋቋሙና የግል ድርጅት ከነበራቸው ፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚነታቸውን ለመቀጠል ወስነው የቀጠሉ፤ እንዲሁም በግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ዐቅድ ያልተሸፈኑ የግል ድርጅት ሠራተኞች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆንም ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል።


ቅጽ 4 ቁጥር 201 ጷጉሜን 5 2014

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች