ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የ2022 የዓለም ኢስላሚክ የፋይናንስ ሽልማትን ተሸለሙ

0
749

ሐሙስ መስከረም 5 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማሻሻል ባደረጉት ጥረት የ2022 የዓለም ኢስላሚክ የፋይናንስ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ “እንደ አገር ዘርፉን አካታች ለማድረግ ስለ ተጓዝናቸው ምዕራፎች ይህንን ሽልማት በመቀበሌ ክብር ይሰማኛል” ብለዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፍ ያካሄደችው ሰፊ ማሻሻያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እያገኘ መሆኑን ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ዕድገትና መሻሻል ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይህ ሽልማት ከዓለም አቀፉ ኢስላሚክ ፋይናንስ አመራር እንደተበረከተላቸውም ተገልጿል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here