በሲጋራ መለኮሻ ላይተር የተነሳ ነፍስ ያጠፋው ግለሰብ እስራት ተፈረደበት

0
1495

የሲጋራ መለኮሻ ላይተር ስጠኝ በሚል በተነሳ ጥል የሰው ሕይወት ያጠፋው ግለሰብ በ8 ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እስራት ተፈረደበት። ተከሳሽ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ሰኔ 19/2011 ከቀኑ 11:00 ሰዓት የሲጋራ መለኮሻ ላይተር ስጠኝ በሚል ከሌላ ግለሰብ ጋር በተነሳ ጥል ተከሳሽ ግለሰቡን በኮብልስቶን ድንጋይ በተቀመጠበት የቀኝ ጭንቅላቱን አንድ ጊዜ በመምታት በራሱ ላይ ጉዳት ማድረሱ እና ሕይወቱ እንዲያልፍ በማድረጉ ተከሶ የነበረ ሲሆን ወንጀሉ የተፈፀመው ልዩ ቦታው መብራት ኃይል ወይም አሎሚስት ግሮሰሪ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ነበር።

ይህንም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት በማረጋገጡ መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽን በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ በማለት ጥቅምት 06/2012 በዋለው ችሎት በ8 ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here