ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በሆነ ወጪ ሕንፃዎችን እያሰገነቡ ነው

0
1013

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአዲስ አበባ በሦስት ክፍለ ከተሞች ከግማሽ ቢሊዮን ብር

በሆነ ወጪ ሕንፃዎችን እያስገነቡ እንደሆኑ አስታወቁ። በ541 ሚሊዮን ብር ወጪ የጋራ መገልገያ ሕንፃዎችን እየተገነቡ የሚገኙት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በጋራ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። በአዲስ አበባ ከተማ በአራዳ ክፍለ ከተማ፣ በአዲስ ከተማ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የጋራ መገልገያ ሕንፃዎችን በመገንባት ከዚህ ቀደም በበርካታ ገንዘብ ከግለሰቦች ሕንፃዎችን በመከራይት ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት ለማስቀረት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ መንግስት ለሕንፃ ኪራይ የሚያወጣውን ወጪም ሙሉ በሙሉ እንደሚያስቀር ታውቋል።

የሕንጻዎች ግንባታ በመንግስት የካፒታል በጀት ድጎማ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን የፊዚካል ስራው አፈፃፀም አራዳ 96ነጥብ 3 በመቶ ፣ አዲስ ከተማ 88በመቶ ንፋስ ስልክ ላፍቶ  50በመቶ የደረሰ ሲሆን የአራዳና የአዲስ ከተማ ህንጻዎች እስከ ታህሳስ  2012  ተጠናቀው ስራ እንደሚጀምሩ ተጠቁሟል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here