ዳሰሳ ዘ ማለዳ ረቡዕ ጥቅምት 12/2012

0
675

1-ጥቅምት 11/2012 ሌሊት በአክቲቪስት ጀዋር መሃመድ መኖሪያ ቤት አጋጠመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ በአምቦ በተቀሰቀሰዉ ግጭት ምክንያት አምስት ሰዎች በጥይት እንደተመቱ የአከባቢዉ ነዋሪዎች የተናገሩ ሲሆን ሕክምና ለማግኘት ወደ አምቦ ሆስፒታል የተወሰዱት ግን ሶስት ሰዎች ብቻ መሆናቸዉን የአምቦ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ደበበ ፈጠነ ተናግረዋል።ለተቃውሞ የወጡትን ሰዎች ለመበተን የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ መጠቀማቸዉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግሯል።(ቢቢሲ)

…………………………………………………………………….

2- የሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ (RAS) ኢትዮጵያን ጨምሮ በተወሰኑ የአፍሪካ አገራት ቢሮውን ለመክፈት ማቀዱን አስታውቋል።የአካዳሚው ምክትል ፕሬዚዳንት ዩሪ ባሌጋ ኢትዮጵያ፣ ዩጋንዳ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ግብፅ ፅህፈት ቤቱን ለመክፈት ያቀደባቸው አገራት መሆናቸውን ተናግረዋል።295 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ አካዳሚ በፈረንጆቹ 1724 የተመሰረተ ሲሆን 125 ሺሕ ሰራተኞች አሉት ከእነዚህም ውስጥ 47 ሺሕ የሚሆኑት ተመራማሪዎች መሆናቸዉ ተገልጿል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

…………………………………………………………………….

3–ጀርመን ለኢትዮጵያ የ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የእርዳታ ለመስጠት ስምምነት ተፈራረመች።ገንዘቡ በኢትዮጵያ ያለውን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለማሳደግ፣ የስራ ፈጠራን ለማስፋት እንዲሁም ከስደት የተመለሱ ዜጎችን ለማቋቋም እንደሚዉል ተገልጿል።በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ሪታ ዋግነር በበኩላቸው የጀርመን መንግስት በቀጣይ ከኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ ጋር በቅርበት ይሰራል ብለዋል።ጀርመን በቀጣይም አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ለመደገፍ ቃል መግባቷንም ተናግረዋል።(ኢቢሲ)

…………………………………………………………………….

 

4-ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ትብብር ገምጋሚ ቡድን “ከደካማ የድንበር ዘለል የፋይናንስ ቁጥጥርና ክትትል ዝርዝር” (ICRG) ክትትል ሒደት መውጣቷን የሰላም ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።ኢትዮጵያ ከዝርዝሩ መዉጣት የቻለችዉ የፋይናንስ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋቷ እንደሆነ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተናግሯል።(ዋልታ)

…………………………………………………………………….

5-አዲስ አበባን ከሀዋሳ የሚያገናኘዉ መንገድ በኦሮሚያ ከተሞች በተቀሰቀሰዉ ግጭት ምክንያት መንገድ በመዘጋቱ ወደ ኹለቱ ከተሞች የሚደረጉ የትራንስፖርት ጉዞዎች መቋረጣቸዉን ታዉቋል።በጥቁር ወሃ ፣ በአርሲ ነገሌና በቡልቡላ ከተሞች አዲስ አበባን ከሀዋሳ የሚገናኘው መንገድ ዛሬ ጥቅምት 11/2012 ረፋድ ጀምሮ በአካባቢው በሚገኙ ወጣቶች በድንጋይና በግንድ በመዘጋቱ መሆኑ ተገልጿል።(ዶቼ ቬሌ)

…………………………………………………………………….

6-ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኒውክለር ኃይልን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል የሚያስችላቸውን የኹለትዮሽ ስምምነት ዛሬ ጥቅምት 12/2012 በሩሲያ ሶቺ   ተፈራረሙ።የኹለትዮሽ ስምምነቱ በሩሲያ ሶቺ እየተካሄደው ካለው የአፍሪካ ሩሲያ የኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን ሲሆን የስምምነቱን  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጌታሁን መኩሪያ(ዶ/ር) ፈርመዉታል።(ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት )

…………………………………………………………………….

7-በሕገወጥ መንገድ የእንስሳት የጠረፍ ንግድ ላይ ያላግባብ የሚጓጓዙትን እንሰሳትን ለማስቀረትና ጠረፍ ላይ የሚገኘውን ኳራንቲ በማጠናከር ከጎረቤት አገር ሱዳን ጋር በጋራ መስራት የሚቻልበትን አሰራር ለመዘርጋት የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ኡመር ሁሴን ከሱዳኑ አቻቸው ጋር ተወያይተዋል።ከጎረቤት አገር ጋር በጋራ የሚሰሩ ስራዎች የጋራ እደገትንና ተጠቃሚነትን ስለሚያመጣ በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚሰራ ሚኒስቴሩ ገልጸዋል።(አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………………….

8-በኢትዮጵያ በ2012 በጀት ዓመት የንፁህ ዉሃ አቅርቦትን ወደ 83 በመቶ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን የውሃ ልማት ኮሚሽን አስታውቋል።በተያዘዉ በጀት ዓመት ከ7 ሚሊዮን 770 ሺሕ በላይ የገጠርና የከተማ ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የውሃ ተቋማት እንደሚገነቡ ኮሚሽኑ ገልጿል።የውሃ ልማት ኮሚሽን የኮሙኒኬሽንና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር  በእደ መላክ እንደተናገሩት በበጀት አመቱ 6 ሚሊየን 84 ሺሕ 193 የሚሆን የገጠርና 1 ሚሊየን 687 ሺሕ 802 የከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የውሃ ተቋማት ይገነባሉ።(ኢቢሲ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here