የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ እንቅስቃሴ ይፋ አደረገ

0
590

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አርሶ አደሮችን በአቅም ግንባታ እና በምርታማነት ዙሪያ ተጠቃሚ የሚያደርግ አዲስ አሰራር ይፋ ማድረጉን አስታወቀ። በዘላቂነት የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አየር መንገዱ ይፋ ያደረገው አዲስ አሰራር ኅብረት ሥራ ዩኒየኖችን በመደገፍ በርካታ አርሶ አደሮችን በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ ስራዎች እንዲታገዙ ለማድረግ እንደሆነ ታውቋል።

በአፍሪካ ግንባር ቀደም የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ ይፋ ባደረገው ድጋፍ፤ ሚሊዮኖችን በግብርና ስራ የሚተዳደሩ አርሶ አደሮችን መድረስ እንደሚችል አስታውቋል። በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወልደ ገብረማሪያም እንደተናገሩት፤ አየር መንገዱ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ በጀመረው አዲስ አካሔድ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። አያይዘውም አርሶ አደሮች ድጋፍ ተደርጎላቸው ምርታቸውን ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚያቀርቡበትን ሁኔታ በማመቻቸት የአርሶ አደሩን የኑሮ ደረጃ ከፍ ማድረግ ዓላማ ተደርጎ እንደሚሰራም ገልፀዋል። አገር በቀል እሴቶችን በማጠናከርም እና ልምዶችንም በማካፈል ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በዘላቂነት ወደ መቀነስ እንዲያመሩ እንደሚደረግ ተወልደ አስታውቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here