መነሻ ገጽዜናየእለት ዜና“ሬድ ፎክስ” በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የግል የመረጃ ማዕከል ሥራ አስጀመረ

“ሬድ ፎክስ” በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የግል የመረጃ ማዕከል ሥራ አስጀመረ

ዕረቡ መስከረም 11 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በ10 ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተቋቁሞ ሥራውን የጀመረው ሬድ ፎክስ ሶሉሽን በተሰኘው የአይሲቲ ኩባንያ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የግል የመረጃ ማዕከል (Data Center) አዲስ አበባ በሚገኘው አይሲቲ ፓርክ ውስጥ በመገንባት በዛሬው ዕለት ሥራ አስጀምሯል።

በዚሁ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይም “ሬድ ፎክስ” ከአሪፍ ፔይ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት መፈጸሙ ተነግሯል።

በየመረጃ ማዕከሉ “ሬድ ፎክስ ሞጁላር ዳታ ሴንተር አንድ” (Red Fox Ethiopia modular Data Center 1) የሚል ስያሜ እንደተሰጠው የገለጹት የ”ሬድ ፎክስ” ዋና ሥራ አስፈፃሚ አዳነ ካሳዬ፤ ተቋሙ መቀመጫውን አዲስአበባ ላይ ቢያደርግም ከኢትዮጵያ ባለፈም በቀጠናው፣ አህጉር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ተቋም የመሆን እቅድ እንዳለው ተናግረዋል።”ሬድ ፎክስ” ፍላጎት ላይ መሠረት ያደረገ አቅርቦት ላይ ትኩሩን አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝም በመግለጽ፤ በቀጣይም በኢትዮጵያ የክልል ከተሞችም ሆነ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ላይ ያሉ የመረጃ ፍላጎቶችን በማየት የመረጃ ማዕከሎችን የመትከል እቅድ መያዙንም ዋና ሥራ አስፈፃሚው አስረድተዋል።

የመረጃ ማዕከሉ በአገር ውስጥ ላሉ ተቋማት አስተማማኝ የመረጃ ማስቀመጫ ቋት እንደሚሆን የተነገረ ሲሆን፤ የጤና ተቋማት፣ የቢዝነስ ተቋማት፣ የመንግስት እና የግል ድርጅቶችን መረጃ ደረጃውን በጠበቀ እና አስተማማኝ በሆነ መንገድ እንደሚያስቀምጥ ተነግሯል።የመረጃ ማዕከሉን መጠቀም የሚፈልጉ ተቋማትም ክፍያቸውን በኢትዮጵያ መገበያያ ገንዘብ በመክፈል አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉም በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች