የታዳጊ ሴቶች ቀን በዓለም ለ8ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ6ኛ ጊዜ ተከበረ

0
295

“ጀግኒት ውጤታማ ታዳጊ ሴቶችን ታበቃለች!” በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል ታዳጊ ልጃገረዶች ክህሎታቸዉን እንዲያዳብሩ፣ እርስ በእርሳቸዉ ልምድ መለዋወጥ እንዲችሉ ለማድረግ በዓለም ለ8ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ6ኛ ጊዜ የታዳጊ ሴቶች ቀን ተከብሯል።

ታዳጊ ልጃገረዶች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን በተመለከተ በጋራ መከላከል እንዲችሉና ኀላፊነት ወስደዉ በትምህርት ቤታቸዉ እና በአካባቢያቸዉ እንዲሠሩ ማድረግን ዓለማው አድረጎ በአሶሳ ከተማ መከበሩ ተገልጿል።

የበዓሉ ክብር እንግዳ በመሆን የግል ተሞክሮአቸውን ለመድረኩ ታሳታፊ ታዳጊ ሴቶች ያካፈሉት ክብርት መዓዛ አሸናፊ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ‹‹ለዉጤታማነቴ ጅማሮ አትችይም ብሎ ያልገደበኝ ቤተሰቤ ነዉ። በልጅነቴ ሐሳቤን በነፃነት የምገልፅ የማልፈራ ልጅ ነበርኩ። ወላጅ እናቴ እንደምትናገረዉ የትምህርት እድሜዬ ሳይደርስ ወደ ትምህርት ቤት የመላኬ ዋነኛ ምክንያት ከኔ ቀድሞ ወደ ትምህርት ቤት የተላከዉ ታላቅ ወንድሜን ሌሎች ተማሪዎች ያስቸግሩት ስለነበር ታናሽ ብሆንም አብሬዉ ብላክ ወንድሜን መከላከል እንደምችል ቤተሰቦቼ በማመናቸዉ ነዉ። ስለዚህ ከልጅነቴ ጀምሮ የሰዉን መብት የማከብር የራሴንም የማላስነካ ነበርኩ።›› በማለት የግል ተሞክሮአቸሁን ለታዳጊ ሴቶች አካፍለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥናት እንደሚያሳየው በዓለማችን አንድ ቢሊዮን ወጣቶች ይገኛሉ። ከእነዚህ ውስጥ 60% ታዳጊ ሴቶች ሲሆኑ፤ በመጭዎቹ 10 ዓመታት ውስጥ የአምራች ኃይሉን ይቀላቀላሉ። ነገር ግን በማደግ ላይ ከሚገኙት ሀገራት 90% የሚሆኑት ታዳጊ ሴቶች ቀጥተኛ ባልሆነ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል። ምክንያቱ ደግሞ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እድገት በሚፈለገው ደረጃ አለመሆን እንደሆነ ይነገራል።

ቅጽ 1 ቁጥር 51 ጥቅምት 15 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here