ለኮማንደር አትሌት ደራረቱ ቱሉ የረዳት ኮሚሽነር ማእረግ ተሰጠ

0
941

ሰኞ መስከረም 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ክብርት ዶክተር ኮማንደር አትሌት ደራረቱ ቱሉ የረዳት ኮሚሽነር ማእረግን ሰጠ፡፡

ኮሚሽኑ በህግ ማስከበር ዘመቻው እና በሥራ አፈፃፀም የላቀ ተግባር ለፈፀሙ የተቋሙ አመራር አባላት እና ሠራተኞች የማበረታቻ ሽልማት እና እውቅና ሰጥቷል፡፡

በማበረታቻ እና የዕውቅና መርኃ ግብሩ ላይ ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ልዩ ተሸላሚ ሆናለች፡፡

በተጨማሪም ኮሚሽኑ በርካታ ጀግኖች አትሌቶችን ላፈሩት አንጋፋው አሰልጣኝ ኮ/ር ሁሴን ሼቦ በረዳት ኮሚሽነርነት ማዕረግ መሾሙ ታውቋል።በመርሐ ግብሩ ላይም የመከላከያ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽነር ጄኔራል ዳመና ዳሮታ፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዴዎን ጢሞቲዎስ፣ የህግ ፍትህ ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እጸገነት መንግስቱና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here