ዳሰሳ ዘ ማለዳ ጥቅምት 17/2012

0
674

1 ከሰሞኑ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ተከስቶ የነበረው የአንበጣ መንጋ በአማራ ክልል በሰብል ላይ ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊ ጉዳት አለማድረሱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። (ቢቢሲ)

………………………………………………………………..

2- ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በብሔራዊ ደረጃ ባካሔደው የደም ልገሳ መርሓ ግብር ለመሰብሰብ አቅዶት ከነበረው 10ሽሕ ከረጢት ደም የ4ሽሕ ከረጢት ጭማሪ በማሳየት 14 ሽሕ ከረጢት ደም መሰብሰቡን አስታውቋል። (ዋልታ)

………………………………………………………………..

3-የዓለም አቀፉ ፓርላማ ለመቻቻል እና ለሰላም ምክር ቤት አራተኛ ጉባኤውን   ጥቅምት 17/2012 በአዲስ አበባ ያካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያም አባል በመሆን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ስምምነት ፈርማለች።የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ተስፋዬ ዳባ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ የመቻቻልና የሰላምና ዓለም አቀፍ የፓርላማ ምክር ቤት 60 አገራትን በአባልነት ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የጠቀሱ ሲሆን ኢትዮጵያም ከምክር ቤቱ የቀረበላትን የአባልነት ጥያቄ እንደተቀበለች ገልጸዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

………………………………………………………………..

4-ጣና ሐይቅን ለመታደግ ሀብት እና ሀሳብን በማቀናጀት ለመጠቀም መዘጋጀታቸዉን የጣና ሐይቅ እና ሌሎች ውኃማ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር አያሌዉ ወንዴ ገልጸዋል።በ2013 አረሙን ሙሉ በሙሉ ለማጽዳት ቅደመ ዝግጅት የተደረገ ሲሆን በሐይቁ ላይ የተበተነው የእንቦጭ አረም ዘርና ቁርጥራጭ መልሶ ሊያገረሽ የሚችል በመሆኑ አረሙን በዚህ ዓመት ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ከተቻለ የስርጭቱን 20 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል ብለዋል።(አብመድ)

………………………………………………………………..

5-የኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከኢንዱስትሪያል ፓርኮች ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች  ከ140 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቋል።የኢንዱስትሪያል ፓርኮች ኤክስፖርት አፈጻጸም ከ2010 በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር የ57 በመቶ እድገት ማሳየቱን በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር መኮንን ሀይሉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ካሉ ዘጠኝ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ከጨርቃጨርቅ እና አልባሳት፣ ቆዳ እና የቆዳ ውጤቶች ፣ኮፐር ኤሌክትሪካል ገመድ፣ ሴራሚክ እና ሌሎች ምርቶችን ኤክስፖርት በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ገቢው የተገኘ መሆኑ አስታዉቀዋል።(ኢቢሲ)

………………………………………………………………..

6-የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል እየደረሰ ላለዉ ግጭት፣ ሞትና መፈናቀል መንግስትን ወቀሰ።ዛሬ ጥቅምት 17/2012 ባወጣዉ መግለጫ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ተቀዳሚ ተግባሩ መሆን እንዳአለበት የገለጸ ሲሆን ይሁን እንጅ በመንግስት በኩል «ችግሮችን የሚያባብስ እንጂ ችግሩን ለመቅረፍ የተወሰደ እርምጃ የለም» ሲል ወቅሷል።መኢአድ « ኢትዮጵያውያን በተወለዱበት ፣ ባደጉበት ፣ሀብት ባፈሩበት ፣ ወልደው በከበዱበት በራሳቸው ሀገር በጠራራ ፀሀይ በአደባባይ ሲገደሉ »መንግስት ህግ አለማስከበሩና የዜጎችን በህይወት የመኖር መብት አለማስጠበቁን በፅኑ ተችቷል።(ዶቼ ቬሌ)

………………………………………………………………..

7-በድሬዳዋ ሰሞኑን ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ምክንያት የተጠረጠሩ 110 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቋል። የፀጥታ ኃይሎች፣ የመንግስት አስተዳድር አካላት እና የከተማዋ ነዋሪዎች ለሰላም በጋራ እየሰሩ ሲሆን በሁከቱ እጃቸው አለበት የተባሉ 110 ተጠርጣሪዎች እስከ ትናንት ድረስ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ እዝቂያስ ታፈሰ ተናግሯል።ዛሬ ጥቅምት 17/2012 ደግሞ የምግብ አቅርቦት የያዙ ኹለት ተሽከርካሪዎች ከቦታው የደረሱ ሲሆን  የህክምና ዕርዳታ የሚያደርግ ቡድንም ወደ አካባቢው መግባቱንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። (አብመድ)

………………………………………………………………..

8- የኢትዮጵያ መንግሥት ከጅቡቲ አቻው ጋር በመነጋገር በጅቡቲ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ብክብር ወደ አገራቸው ለመመለስ እየሰራ እንደሆነ አስታወቀ። በጅቡቲ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አብዱልአዚዝ መሐመድ  ጥቅምት 17/2012 ታጁራ እና ኦቦክ በተሰኙ  የስራ ጉብኝት አካሂደዋል።በሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጤንነታቸውና ክብራቸውን ተጠብቆ ወደ አገራቸው በፍቃደኝነት እንዲመለሱ ከኤምባሲው ጋር በመሆን የጅቡቲ መንግስት በተለይም የኦቦክ መስተዳድር እና በጅቡቲ ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።በአሁኑ ወቅት በጣቢያው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በፈቃደቸው ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ በተመለከተም ከኃላፊዎቹ ጋር ተወያይተዋል።(ኢቢሲ)

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here