የዘንድሮው መውሊድ በዓል “የእዝነቱ ነቢይ” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገልጿል
አርብ መስከረም 27 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1 ሺሕ 497 ዓመት የነብዩ መሐመድ መውሊድን በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
በመልዕክቱም “የነብዩ መሐመድ ፈለግን በመከተል ስብዕናቸውን በመላበስ ወደ ሰላም የሚወስዱ መልካም ተግባራትን ማከናወን ይግባል” ብሏል።
የዘንድሮው መውሊድ ነብዩ ሙሀመድ ለመላው ዓለም የተላኩ በመሆናቸው የእሳቸውን ልህቀት በሚገልፅ መልኩ “የእዝነቱ ነቢይ” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር አስታውቋል።
ነብዩ ሙሀመድ ሀበሻን ከእቅፍ እስከ ህልፈታቸው ድረስ በልዩ ኹኔታ ያውቋት ነበር ያለው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ በዚህ ምክንያት መውሊድ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዘንድ የሚከበረው በልዩ ክብርና ኩራት መሆኑን መግለጹን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡
መውሊድ ኹሉም የተቸገሩ ዜጎች የሚረዱበት እንዲሆን የጠየቀው ምክር ቤቱ፤ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን አስተላልፏል።



