በመዲናዋ ከ7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ኹለት ሜጋ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው

0
845

በአዲስ አበባ ከ7 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ኹለት ሜጋ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ለማካሄድ ስምምነት ተፈረመ። የመጀመሪያው ከ6 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ኹለት ፕሮጀክቶችና በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አንድ ፕሮጀክት፣ የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከል ግንባታ ነው ተብሏል።

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በመዲናዋ አስተማማኝ የግብርና ምርት አቅርቦት እንዲኖር የሚያግዝና ገበያውን በማረጋጋት ለአምራቹ እና ለሸማቹ ተመጣጣኝ ምርቶች እንዲቀርቡ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል።

ኹለተኛው በ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በሆነ ወጪ የሚገነባው የዘውዲቱ ሆስፒታል ማስፋፊያ የB+G+8 ፕሮጀክት ግንባታ መሆኑ ተመላክቷል። ግንባታው 200 ሕሙማንን የሚያስተናግዱ አልጋዎች፣ 27 የድንገተኛ ሕክምና መስጫ ክፍሎች እንዲሁም የቀዶ ጥገናና የፊዚዮቴራፒ ሕክምናዎችን ጨምሮ የስብሰባ አዳራሾችን ያካተተ መሆኑን ነው የከተማ አስተዳደሩ ያስታወቀው።

ፕሮጀክቶቹ ኦቪድ ግሩፕ እና በተስፋዬ ኃይሌ ኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ይገነባሉ መባሉንም ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል።


ቅጽ 4 ቁጥር 205 መስከረም 28 2015

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here