ምንጭ፡-ቢቢሲ (2021)
ዩክሬን በዓለም በስንዴ አምራችነታቸው ቀዳሚ ከሆኑ አገራት አንዷ መሆኗ ይነገራል። በአሁኑ ወቅትም አገሪቱ ከሩስያ ጋር በገባችበት ጦርነት ሳቢያ ዓለም ዐቀፍ የምግብ ቀውስ እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑ ይጠቀሳል።
በርካታ አገራት ከዩክሬን ስንዴ የሚሸምቱ ሲሆን ግብጽ በቀዳሚነት በዓመት ከሦስት ሚሊዮን ቶን በላይ ስንዴ ትገዛለች። ኢንዶኔዥያና ባንግላዲሽም ባለፈው የፈረንጆቹ 2021 በተከታታይ መጠኑ ከፍ ያለ ስንዴ ከዩክሬን የሚገዙ አገራት ሆነው ተቀምጠዋል።
በዓመቱ ከዩክሬን ከፍተኛ የስንዴ ምርት መጠን ግዢ ከሚፈጸሙ ዐስር አገራት መካከል ስድስቱ ከአፍሪካ መሆናቸውም ተመላክቷል።
የመን ከአፍሪካ በቀዳሚነት ከአንድ ሚሊዮን ቶን በላይ ስንዴ ከዩክሬን የገዛች ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በስድስተኛ ደረጃ ከዓለም በዐስረኛ ደረጃ 680 ሺሕ ቶን ገደማ የገዛች አገር ሆናለች። ኢትዮጵያ በፈረንጆች 2023 ስንዴ ወደ አገር ላለማስገባት በተቃራኒውም ወደ ውጭ ገበያ ለመላክ ማቀዷ ይታወቃል።
ቅጽ 4 ቁጥር 206 ጥቅምት 5 2015



