ባለስልጣኑ የትራማዶል መድሀኒት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ

0
1335

ማክሰኞ ጥቅምት 22 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን የትራማዶል መድሀኒት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ባለስልጣኑ በመድሀኒቱ አጠቃቀም ዙሪያ በሰጠው መግለጫ፤ ከጤና ባለሙያ ትዕዛዝ ውጭ በርካታ አፍላ ወጣቶች ለህመም ማስታገሻ በሚል ያለአግባብ እንደሚጠቀሙት መረጃ እንደደረሰው አስታውቋል።

መድሀኒቱ ያለማዘዣ ከሚሰጡ መድሀኒቶች ውስጥ አንዱ እንደነበር የገለፀው ባለስልጣኑ፤ የመድሐኒቱን ሱስ የሚያስይዝ ባህሪ ከግምት ውስጥ በማስገባት ያለማዘዣ ከሚታዘዙ መድሀኒቶች ዝርዝር ውስጥ ለማውጣት የተለያዩ ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል።ለዚህም የኹኔታውን አሳሳቢነት ግምት ውስጥ በማስገባት በመድሀኒቱ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ እንደሆነ ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

መድሃኒቱ ለጤናው ዘርፍ መሰረታዊ መድሀኒት በመሆኑ ከዚህ በኋላ በልዩ ማዘዣ ወረቀት እንደሚታዘዝ እና የመድሃኒቱ ማዘዣም ቁጥጥር እንደሚደረግበት ነው የተገለጸው።

የመድሃኒት ችርቻሮ ድርጅቶችና የጤና ተቋማት በመድሃኒቱ አጠቃቀም ላይ በየጊዜው ሪፖርት እንዲያቀርቡ ይደረጋልም መባሉን ኤፍ ቢሲ ዘግቧል።

ባለሰልጣኑ መድሀኒቱን አለግባብ የሚሸጡ፣ የሚያሰራጩ እና የሚጠቀሙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድም አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here