በኢትዮጵያ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 29.7 ሚሊዮን ዜጎች እንዳሉ ዩኒሴፍ አስታወቀ

0
558

የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት ፈንድ (ዩኒሴፍ) በኢትዮጵያ 29.7 ሚሊዮን ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የገለጸ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 12.5 ሚሊዮኑ ሕጻናት እንደሆኑ አስታውቋል።

ዩኒሴፍ በሪፖርቱ 2.75 ሚሊዮን ዜጎች መፈናቀል አጋጥሟቸዋል ያለ ሲሆን፣ 875 ሺሕ 879 የሌሎች አገራት ስደተኞችም በኢትዮጵያ እንደሚገኙ አስታውቋል።

በሦስተኛው ዙር ጦርነትም ከአማራ ትግራይ እንዲሁም አፋር ክልሎች 574 ሺሕ ሕዝብ እንደተፈናቀለ የተገለጸ ሲሆን፣ በሦስቱ ክልሎች ለ23 ሺሕ 62 ሕጻናትና ሴቶች በዩኒሴፍ የመጀመሪያ የሕክምና እርዳታ እንደተደረገለቸውም ታውቋል።

እየተጠናቀቀ ባለው 2022 በኢትዮጵያ አስፈላጊ የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ 532.3 ሚሊዮን ዶላር የሚፈለግ የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ሪፖርት እስከ ወጣበት ቀን ድረስ 201.6 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ተገኝቷል። ይህም ከሚያስፈለገው የገንዘብ መጠን 38 በመቶውን ብቻ ማለት ነው። በ2021 አስፈልጎ ከነበረው የገንዘብ መጠንም የ281 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ እንዳሳየም በሪፖርቱ ተመላክቷል።


ቅጽ 5 ቁጥር 209 ጥቅምት 26 2015

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here