ረቡዕ ጥቅምት 30 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የታላቁ ደራሲና ጋዜጠኛ የበአሉ ግርማ ባለቤት አልማዝ ዛሬ ጥቅምት 30/2015 ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው አርድተውኛል ሲል ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ አስታውቋል።
አልማዝ ባለቤታቸውን የበአሉ ግርማን ሞትና መሰወር አልቀበል ብለው የቆዩ ሲሆን፤ ሁልግዜ ጠዋት ላይ ቤታቸውን አፀዳድተው በር ከፍተው በአሉ ግርማን ይመጣል እያሉ ሲጠብቁት ኖረው በዛሬው ዕለት ህይወታቸው አልፏል።
አልማዝ አበራ ከደራሲ በአሉ ግርማ ያፈሯቸው የሦስት ልጆች እናት ነበሩ።



