የመስኖ ፕሮጀክቶችን በሚመለከት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሰጧቸው ምላሾች

0
842

ማክሰኞ ኀዳር 6 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የመስኖ ፕሮጀክቶችን እና የከርሰ ምድር ውኃን አውጥቶ መጠቀምን በሚመለከት በተለያዩ ክልሎች እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡

በዚህ መሠረት፦

👉በሶማሌ ክልል ሺኒሌ ላይ
👉በአፋር ክልል የሱኑታ ፕሮጀክት
👉በኦሮሚያ ክልል በቦረና
👉በአማራ ክልል ቆቦና ግራር
👉በደቡብ ክልል ሦስት ቦታ
👉በበሲዳማ ክልል አንድ ቦታ የጥልቅ የውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ነው፡፡

ይሄ በከተሞች ላይ የሚሠራውን አይመለከትም ያሉ ሲሆን፤ ለአብነትም በጎንደር የከተማውን የውኃ ችግር ለመፍታት እየተሠራ ያለውን ሥራ አንስተዋል፡፡ ለጎንደር ከተማ የውኃ ችግርን ለመቅረፍ ከ10 ዓመት በፊት የተጀመረው ግድብ ፕሮጀክቱ ችግር ያለበት በመሆኑ ፈርሰው መሠራት ያለባቸው ሥራዎች አጋጥመዋል ብለዋል፡፡ እስከዛ ሕዝቡ እንዳይቸገር ሌሎች ፕሮጀክቶች መጀመራቸውንም ገልጸዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here