ዳሰሳ ዘ ማለዳ ጥቅምት 24/2012

0
554

1- ከጥቅምት12 እስከ 24/2012 ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ 14 ያህል ነጥቦችን ያካተተ መግለጫ አውጥቷል።በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የተለያዬ ቋንቋ ተናጋሪዎች በብዛት እንደሚገኙ ያመለከተው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ “የቤተ ክርስቲያኒቱን ተከታዮች በቋንቋቸው ማስተማርና ማገልገል እንዲቻል በየአሕጉረ ስብከቶቹ የሚገኙ የአብነት ትምህርት ቤቶችን ማጠናከር፣ ከልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች አገልጋዮችን ማፍራት እንዲቻል ለትምህርት ቤቶች ማጠናከሪያ የሚሆን ቋሚ በጀት እንዲመደብ፤ በቀጣይም በሁሉም አፍ መፍቻ ቋንቋ በማዕከል ማሰልጠኛ እንዲቋቋም” ዉሳኔ አስተላልፏል።(አብመድ)
……………………………………………………………..
2የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ የምርጫ ቅስቀሳውን ማድረግ መጀመሩን አስታዉቋል።ፓርቲው በአዲስ አበባ የሚገኙ በርካታ የምርጫ ወረዳዎችን ባሳተፈ መልኩ ሕዝባዊ ውይይት ማድረጉን የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ናትናኤል ፈለቀ ገልጸዋል።ፓርቲው ከ400 በላይ በሚሆኑ የምርጫ መረጃዎች በየሳምንቱ የውይይት መድረክ በማዘጋጀት ውይይት እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።(አሀዱ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን )
……………………………………………………………..
3-ከሳምንት በፊት በኦሮሚያና በሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ ተከስቶ ከነበረው ግጭት ምክንያት የሞቱት ሰዎች ብዛት 86 መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።ጥቅምት 23/2012 በሰጡት መግለጫ”ያለፉ ስህተቶች ለማረም እየሰራን በሌላ በኩል ደግሞ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ ሕጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ እንወስዳለን” በማለት በድርጊቱ ውስጥ እጃቸው ያለ ሰዎች ሁሉም በጥፋታቸው መጠን ተጠያቂ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።(ቢቢሲ)
……………………………………………………………..
4-ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ 791 የሳይበር ጥቃቶች መፈጸማቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ አስታወቀ።ዓለም በሳይበር ምህዳር አንድ መንደር በሆነችበት በዚህ ዘመን የሳይበር ኃይል ከገንዘብ፣ ከጦር መሳሪያ እና መሰል አቅሞች በላይ የሆነ የዘመናችን ቁልፍ መወዳደሪያ አቅም መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዘይኑ ጀማል ተናግረዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)
……………………………………………………………..
5-የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ2010 ሊያስገነባው አቅዶ ለነበረዉ ባለአምስት ወለል የመማሪያ ክፍል ግንባታ ፕሮጀክት በጨረታ አሸናፊ ለሆነው“ሼድ ኮንስትራክሽን” ለተባለ የስራ ተቋራጭ 24 ሚሊዮን 923 ሺሕ 660 ብር ቅድመ ክፍያ የፈፀመ ቢሆንም ግንባታው እስካሁን ያልተጀመረ ሲሆን ተቋራጩም እስካሁን ያለበት አድራሻ አለመታወቁን የኮንስትራክሽን ስራዎቸ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን አስታወቋል።(ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
……………………………………………………………..
6-የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ ጥቅምት 26 እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።ህዳር 10/2012 ለሚካሄደው የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጠት የሚፈልጉ ዜጎች ከጥቅምት 26 እስከ ህዳር 6/2012 ባሉት 10 ቀናት መመዝገብ ያለባቸው መሆኑን ቦርዱ አስታውቋል ።(ፋና ብሮድካስቲንግ)
……………………………………………………………..
7-በኢትዮጵያ በተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ምክንያት ዜጎች በርሃብ የሚጠቁ ሲሆን ይህንን ችግር ለመፍታት የኢትዮጵያ ብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንና የዓለም የምግብ ፕሮግራም በጋራ በመሆን በፈረንጆቹ 2030 ከተያዙ 17 ዘላቂ የልማት ግቦች መካከል አንዱ የሆነው ግብ 2 ረሃብን ዜሮ የማድረግ አላማን ለማሳካት በአዲስ አበባ ከተለያዩ የዓለም አገራት ከመጡ 170 ተሳታፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።(ዋልታ)
……………………………………………………………..
8-በስልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ ቀበሌ 01 ጥቅምት 23/2012 ረፋድ ላይ በደረሰዉ የእሳት አደጋ 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የወረዳው ዋና አስተዳደሪ ከድር መሐመድ አስታዉቀዋል።መነሻ ምክንያቱ ባልታወቀው በዚህ የእሳት ቃጠሎ 11 ሱቆችና የተለያዩ ድርጅቶች ያሉበት ሕንጻ ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በስፍራው የሚገኘው የወረዳ የነዳጅ ማከፋፈያ የንግድ ተቋምና ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች ጉዳቱ ከፍ እንዲል እንዳደረጉት ገልጸዋል።(ኢቢሲ)
……………………………………………………………..
9-ከተጀመረ ሶስት ዓመታትን ያስቆጠረዉ በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ የኮተቤ – አራራት ሆቴል መንገድ ግንባታ በመጓጓተቱ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን አሰምተዋል።ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተያዘለት የኮተቤ – አራራት ሆቴል መንገድ ግንባታ ከመቆፈር ውጪ ምንም አይነት ግንባታ ባለመካሄዱ በነዋሪዎቹ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ እንግልት አድርሷል። የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጥዑማይ ወልደገብርኤል በበኩላቸው ኅብረተሰቡ ያነሱት ቅሬታ ተገቢ መሆኑን ገልጸው አንድ አመት ከወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ ችግር ሲሆን ሌላው ግን ከተቋራጮቹ ድክመት የተነሳ መጓተቱን ተናግረዋል።(ዋልታ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here