የሰብዓዊ መብቶች ትምህርትን በመደበኛና መደበኛ ባልሆኑ የትምህርት ስርዓቶች ውስጥ ማካተት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

0
901

አርብ ጥር ቀን 26 2015 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የትምህርት ሚኒስቴር የሰብዓዊ መብቶች ትምህርትን በመደበኛና መደበኛ ባልሆኑ የትምህርት ስርዓቶች ውስጥ ማካተት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ዋና ኮሚሽነር ዳኤንል በቀለ (ዶ/ር) ፈርመዋል፡፡

የስምምነቱ ዋና አላማ ኹለቱም ተቋማት ያለባቸውን የጋራ ሃላፊነት ለመወጣት እና የሰብዓዊ መብት እሴቶችን ወደ ማሕበረሰቡ ማስረጽ ለማስቻል ነው ተብሏል።

ይህን ስምምነት ትምህርት ቤቶችም በመደበኛው እና ከመደበኛው ውጭ በሆነ መንገድ ተደራሽ ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸውንም መግለጫው አመላክቷል።

ስምምነቱ የሰብዓዊ መብቶችን በተመለከተ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ከመፍጠር አንጻር ትልቅ አስተዋጽዖ እንዳለው ዋና ኮሚሽነሩ አንስተዋል።

በሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ሲጣሱ የሚስተዋሉ የሰብዓዊ መብቶች የሚከበሩበትና በሰብዓዊ መብት ውጤታማ ለመሆንም በትምህርት ስርዓቱ እንዲካተት መድረጉ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ በበኩላቸው÷ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እንዲሁም መብትና ግዴታውን የሚያውቅ ዜጋ ለመፍጠር ስምምነቱ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ማለታቸውን ፋብኮ ዘግቧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here