በደቡብ አፍሪካ ሕክምና ለተከለከለችው ኢትዮጵያዊቷ የኩላሊት ታማሚ የገቢ ማሰባሰቢያ ሊደረግ ነዉ

0
713

በደቡብ አፍሪካ የኩላሊት ሕክምና እንዳታደርግ ለተከለከለችው ኢትዮጵያዊቷ ዓለም ኤርሴሎ፤ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የሦስት ቀን ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ጀምረዋል። ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላት ኢትዮጵያዊቷ ዓለም በደረሰባት የኩላሊት ሕመም በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበረግ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ስታገኝ የነበረ ሲሆን የደቡብ አፍሪካ ዜግነትም ሆነ የመኖሪያ ፈቃድ ስለሌላት ሕክምና እንዳታገኝ መደረጉ ይታወሳል። ለሦስት ቀናት በሚካሔደው በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ የሚገኘው ድጋፍ ታማሚዋ በግል የሕክምና ተቋም ሕክምናውን እንድታገኝ የሚያስችል መሆኑም ታዉቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here