የሚዲያ ተቋማት በፖሊሲ ደረጃ ጠንካራ የይለፍ ቃል ሊኖራቸው እንደሚገባ ተጠቆመ

0
467

የጋዜጠኝነት ምሕዳር ወደ ሳይበር እየተቀየረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የመገናኛ ብዙኃን በፖሊሲ ደረጃ ጠንካራ ይለፍ ቃል ፣ ጠንካራ ባለሙያ እና መመስጠሪያ እንዲኖራቸው እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ። በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ አዘጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ እየተካሔደ በሚገኘው የሳይበር ደኅንነት ማስጨበጫ ሳምንት ለመገናኛ ብዙኃን የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር ተካሒዷል።

በዚህ ዝግጅት ላይም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፋክሊቲ የሳይበር ደህንነት አስተባባሪ  ነብያት ፍቅሩ የመገናኛ ብዙኃን ምህዳራቸውን በማስፋት ወደ ሳይበር በመግባታቸው ጠንካራ ይለፍ ቃል እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል። ነብያት አያይዘውም ከይለፍ ቃሉም በተጨማሪ ተቋማቱ በየጊዜው ድረ ገፃቸውን ኦዲት ማስደረግ እንደሚኖርባቸውም ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ጋዜጠኞች የሀገርን ደህንነት ከማስጠበቅ አንጻር የህብረተሰቡን ንቃተ-ህሊና የማሳደግ ሚናቸውን ሊወጡ እና በሚደርሱ ጥቃቶች አዘጋገብ ዙሪያ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ  ነቢያት አሳስበዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here