በድሬዳዋ ለደረሰው ግጭት የተሳሳቱ መረጃዎች ዋነኛ ምክንያት ናቸው

0
233

በቅርቡ በድሬዳዋ ተከስቶ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ላደረሰው ግጭት መነሻ በዋነኛነት ተሳሳቱ ምረጃዎች ወደ ግለሰቦች መድረሳቸው መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አስታወቀ። ምክር ቤቱ 43ኛ መደበኛ ጉባዔውን ያካሔደ ሲሆን በጉባዔውም ላይ ከተማዋን ሰላም በሚመለከት ሰፊ ውይይት ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል።

በጉባዔው ላይ በተለያዩ ጊዜያት በማኅበራዊ ድህረ ገጾችም ሆነ በተወሰኑ ቡድኖች የሚነዙ የተሳሳቱ መረጃዎች ሳቢያ የአስተዳደሩ ነዋሪ ሰላሙን እንዲያጣ አይነተኛ ሚና መጫወቱን የተናገሩት የአስተዳደሩ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፈጡም ሙስጠፋ አመራሩ ይሄንን እታች ድረስ ወርዶ በማጣራትና ትክክለኛ መረጃን ለኅብረተሰቡ በመስጠት ህዝቡን የማረጋጋት ስራ እንዲሰሩ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

በድሬዳዋ በተከሰቱት ግጭቶች እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ በቁጥጥር ስር የዋሉ110 ሰዎች መኖራቸው በሪፖርቱ የተገለጸ ሲሆን በማስረጃ በተደገፈ ምርመራ 51 ተጠርጣሪዎች ተለይተው በልዩ ሁኔታ እየተመረመሩ እንደሚገኙና በቀጣይም የምርመራው ሂደቱን ውጤት በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here