አህጉራዊ ነጻ ዝውውር ስምምነት እንዲተገበር የ 15 አገራት ድጋፍ ተጠየቀ

0
505

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን 3ተኛው የስደተኞች፣ የስደት መጠለያ የሚገኙ ስደተኞች እና የአገራት የውስጥ መፈናቀሎች ላይ የሚመክረው ጉባኤ በአዲስ አበባ በማካሔድ ላይ ሲሆን አገራት የተሻለች አፍሪካን ለመፍጠር የዜጎቻቻውን ነፃ ዝውውር እንዲተገብሩ ተጠየቀ።

የአባል ሀገራቱ ዜጎች አፍሪካዊያን ነጻ ዝውውር እንዲያደርጉ የሚያስችለውን ስምምነት እንዲተገበር ቁርጠኝነት ሊኖር እንደሚገባም ተመላክቷል።
በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የተቀመጠውን አቅጣጫ ለመተግበር እንዲያስችል በማሊ የአፍሪካ የስደተኞች የምርምር እና ጥናት ማዕከል ለመመሥረት በሂደት ላይ እንደሚገኝ ለዚህም የማሊ፣ ሞሮኮ ና ሱዳን መንግሥታት በጋራ እየሠሩ እንደሚገኙ በአፍሪካ ህብረት ኮምሽን የማህበራዊ ጉዳይ ኮምሽነር አሚራ ኤልፋድል ይፋ አድርገዋል። በተመሳሳይ ሕገ ወጥ ስደትን ለመከላከል የአፍሪካውያን ስደተኞች መቆጣጠሪያ በሞሮኮ እና አህጉራዊ ኦፕሬሽን ማዕከል በካርቱም ይቋቋማል ተብሏል።

የሕግና የአሰራር ፍኖተ ካርታዎች ለሚተገበሩ ሥራዎችን ማሳለጥ የህብረቱን ውሳኔ አንድ እርምጃ ወደፊት ለመውሰድ የሚጠቅሙ መሆናቸው በጉባኤው የተገኙ አባል አገራት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ሩዋንዳ በበኩሏ በሀገሪቱ መጠለል ለሚፈልጉ ስደተኞች በማመቻቸት 189 ስደተኞችን ተቀብላለችም ብለዋል። በቀጣይነትም በርካታ ስደተኞችን ለመቀበል በመዘጋጀት ላይ መሆኗን ገልጻለች።

አፍሪካውያን በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ በመፍቀድ ለነጻ የንግድ ትስስር ስኬት አገራት ሚናቸውን ሊጫወቱ እንደሚገና ተመልክቷል። የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ነጻ ዝውውር ነጻ የንግድ ቀጠና ዝውውር ግቡን እንዲያሳካ የታሰበበት ነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 53 ጥቅምት 29 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here