በአፋር ክልል የብልፅግና ፓርቲ የወረዳ አመራር ተገደሉ

0
735

ሰኞ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ከአዳማ ወደ አዋሽ በሚወስደው መንገድ ላይ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ሚያዚያ 28/2015 በተከፈተ ተኩስ በአፋር ክልል በገቢ ረሱ የሓንሩካ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ጽ/ቤት ኃላፊ ኡመር ለማ መገደላቸውን የአፋር ክልል የብፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት አሳውቋል።

ኡመር “አሸባሪዎች በከፈቱት ተኩስ” ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፤ በኃላፊው ድንገተኛ ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

ጽሕፈት ቤቱ ስለጥቃት አድራሾቹ ማንነት፣ ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት በሌሎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱና ስለተወሰደው እርምጃ በዝርዝር የገለጸው ነገር የለም።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here