ሰኞ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በቅርቡ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሰጣቸው የኮሌጁ ፕሮፌሰሮች በሕይወት ዘመናቸው በአካዳሚክ፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በዛሬው ዕለት ዕውቅና ሰጥቷል፡፡
በኮሌጁ ዕውቅና የተሰጣቸው ፕሮፌሰር አበራ ቁሜ፣ ፕሮፌሰር ምትኬ ሞላ፣ ፕሮፌሰር ግርማ ስዩም እና ፕሮፌሰር የወርቅአበባ አበበ ሲሆኑ፣ የአካዳሚክ፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ተሞክሯቸው ለኮሌጁ ማሕበረሰብ አካፍለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አንዱአለም ደነቀ ለፕሮፌሰሮቹ የተዘጋጀላቸውን የዕውቅና ሰርተፍኬት ከሰጡ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ‹‹የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በአገራችን በርካታ ፕሮፌሰሮችን በማፍራት ረገድ ቀዳሚ ነው፡፡›› ብለዋ
ዛሬ ዕውቅና የተሰጣቸው ፕሮፌሰሮችም ለኮሌጁ እና ለአገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ጠቁመው፣ በቀጣይም ይህንኑ አበርክቷቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አደራ ማለታቸውን ከኮሌጁ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡



