ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ አገኘ

0
530

ሐሙስ ግንቦት 3 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ተሰማርቶ በመስራት ላይ የሚገኘው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፤ የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝቷል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ፤ ባንኩ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድን ለሳፋሪ ኮም መስጠቱን አስታውቀዋል፡፡

ይህም ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው የውጭ አገር ኩባንያ እንደሚያደርገው የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመለክታል፡፡

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ሳምንታት የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ይጠበቃል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here