አይ.ኤም.ኤፍ የኢትዮጵያ ፕሮግራም የአበዳሪዎችን ዋስትና እንደሚፈልግ አስታወቀ

0
545

ቅዳሜ ግንቦት 5 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር እየተወያየ ሲሆን፤ የትኛውም አዲስ ፕሮግራም የአበዳሪዎችን ዋስትና እንደሚያስፈልግ የተቋሙ ቃል አቀባይ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

አይ.ኤም.ኤፍ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ዘላቂ ሰላምን ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት ለማሳለጥ፣ “የአገር ውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳዎችን ተቀብሏል” ሲሉ ቃል አቀባይዋ ጁሊ ኮዛክ ተናግረዋል፡፡

በ2021 መጀመሪያ ላይ ኢትዮጵያ በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ ብድር ለማግኘት እንደጠየቀች ያስታወሰው ዘገባው፤ ኢትዮጵያ ከአይ.ኤም.ኤፍ ቢያንስ 2 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር ድርድር ላይ ነች ብሏል።

የሰሜኑን ጦርነት ጨምሮ በተከሰቱ ግጭቶች ከፍተኛ ጫና የደረሰበትን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከከፋ ውድቀት ለማዳን ባለሥልጣናት ከአበዳሪዎች ጋር ተከታታይ ድርድር ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአሁኑ ወቅት በውጭ ምንዛሬ፣ በዋጋ ንረትና በውጭ ዕዳ ጫና አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን የዘርፉ ምሁራን ሲገልጹ ይደመጣል፡፡ ይሁን እንጂ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱም ይሁን የዋጋ ንረቱ መፍትሔ ሳይገኝለት አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here