በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው ግጭት የተጠረጠሩ 13 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

0
471

የኹለት ተማሪዎችን ሕይወት በቀጠፈው በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው ግጭት የተጠረጠሩ 13 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታወቀ። በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር መግለጫ መሰረት፣ በግጭቱ ላይ እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 13 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሔደባቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ጥቅምት 29/ 2012 ምሽት 5:00 ስዓት ላይ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የኹለት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉን እና ሌሎች 13 ተማሪዎች ላይም ቀላል የሚባል ጉዳት መድረሱን ያረጋገጠው የዩንቨርሲቲው አስተዳደር፣ የሠራተኞቹን እንዲሁም የተማሪዎቹን እና የአካባቢውን ማህበረሰብ ያሳዘነ ድርጊት መሆኑን በመግለፅ ክስተቱን አውግዟል።

በሌላ በኩል የዲኖች ስብስብ ያለበት ግብረ ኀይል ማቋቋሙን የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፣ ተማሪዎችን የማረጋጋት እና ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎችን በመከታተል በወቅቱ ህክምና እንዲያገኙ የማስተባበር ሥራ እየተሠራ መሆኑን አስታውቋል። በአሁኑ ሰዓትም በወልድያ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ጉዳቱ ከደረሰባቸው መካከል 11 ተማሪዎች ዛሬ ከሆስፒታል ወጥተዋል።

በተጨማሪም እንደ ዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ገለፃ ሕይወታቸው ያለፋ ተማሪዎች የቀበሌም ሆነ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ መሆናቸውን የሚገልፅ ምንም አይነት መረጃ በኪሳቸው ባለመገኘቱ፣ እንዲሁም ህንፃ ቁጥሩንና የዶርም ቁጥሩን መለየት ባለመቻሉ የተማሪዎቹን ማንነት ለመለየት ጊዜ የወሰደ ቢሆንም የተቋቋመው ግብረ ኀይል ሕይወታቸው ያለፉት የዩኒቨርሲቲው ተማሪ መሆናቸውን አረጋግጧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here