የኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋም እና መገንባት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

0
301

ሰኞ ሰኔ 5 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋም እና መገንባት የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የምክክር መድረኩ ዓላማ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በተካሔደው ጦርነት ሳቢያ የደረሰውን ጉዳትና መልሶ ማቋቋም የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ላይ ምክክር በማድረግ ሰው ተኮር ልማት ለማጠናከርና ማህበራዊ ግንኙነትን ለማደስ እንደሆነ ተገልጿል።

የደረሰውን ጉዳትና መልሶ ማቋቋም ፍላጎት የዳሰሳ ጥናት በሸፈናቸው ክልሎች አጠቃላይ 22 ነጥብ 69 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ውድመት መድረሱን ነው የተጠቆመው።

በማህበራዊ፣ በምርት፣ በመሰረተ ልማት፣ እና ባለብዙ ዘርፎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጾ፤ ለመልሶ ግንባታና ማቋቋም ጥረት እንደሚያስፈልግም ተነግሯል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በዓለም ባንክ እና የልማት አጋሮች የቴክኒክ ድጋፍ በመታገዝ ግጭቱ ያደረሰውን ውድመትና ጥፋት እንዲሁም የፈጠረውን ፍላጎት አካታች መረጃ ለመስጠት የጉዳት ፍላጎት ግምገማ ማድረኩም መካሄዱ ተመላክቷል።

በምክክር መድረኩ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ ሚኒስትሮች፣ በኢትዮጵያ የአገራት አምባሳደሮች፣ የልማት አጋሮች፣ የተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ተወካዮች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here