ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

0
402

ሰኞ ሰኔ 5 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ፡፡

ሌተናል ጄነራል ይልማ የቀድሞ የአየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄን በመተካት ነው የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢነት የተሾሙት፡፡

ሌተናል ጄነራል ይልማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሥራ አመራር ቦርድ አባል ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡ግርማ ዋቄ ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here