የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) በወልዲያ ተማሪዎች ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ

0
1253

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ጥቅምት 29/2012 በወልዲያ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የተፈፀመዉን የግድያ ወንጀል እና ድብደባ አወገዘ።

ኦፌኮ ‹‹የነገን ወጣት ትውልድ በመግደል ደም በማፍሰስ እና ሕዝብን አጋጭቶ ሥልጣን ለመያዝ የሚደረገው ሩጫ ይቁም!›› ሲል ባወጣው መግለጫ፤ ‹‹በሕገ ወጦች የተፈጸመውን የተማሪዎች ድብደባ እና እገታን ፓርቲያችን አጥብቆ ያወግዛል›› ሲል አክሏል።

ሕዝብን እርስ በርስ በማጋጨት በማፈናቀል በአቋራጭ ሥልጣን ለመያዝ የሚደረገዉ ጥረት፣ የአገሪቱን ሕዝቦች ወደ ሌላ የማያባራ የእርስ በርስ ግጭት የሚያመራ በመሆኑ ወንጀለኞቹን በመያዝ ተገቢዉን ቅጣት እንዲያገኙ ፓርቲዉ ጠይቋል። ለዚህ እኩይ ድርጊት አጸፋ ለመመለስ በሚል ሌላ ግጭት እንዳይፈጠርም ጥንቃቄ እንዲደረግ ሲል አሰስቧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here