የገቢዎች ሚኒስቴር በጥቅምት ወር ብቻ 32 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ግብር በመሰብሰብ የእቅዱን 97 ነጥብ 6 በመቶ ማሳካቱን አስታወቀ። ይህ አፈፃፀም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ተገልጿል።
የገቢዎች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሠራተኞች በቅንነት፤ በትጋት፣ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠትና ከሥራ ሰዓት ዉጪ ጭምር ጊዜያቸዉን መስዋዕት አድርገዉ በመሥራታቸዉ እንዲሁም ግብር ከፋዩም ታማኝ አገር ወዳድ ዜጋ በመሆን ግብሩን እየከፈለ መምጣቱ ባለፉት ወራት ለታየው ጭማሪ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።
የገቢዎች ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ በሦስት ወራት ውስጥ 56 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 57 ቢሊዮን ብር ግብር የሰበሰበ ሲሆን፣ የዕቅዱን 102 በመቶ ማሳካት መቻሉን ማስታወቁም ይታወሳል።



