የስምንት ዓመት ሕጻን መደፈሯን ተከትሎ በደላንታ ወረዳ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

0
715

አርብ ሰኔ 16 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በአንዲት የስምንት ዓመት ሕጻን ልጅ መደፈሯን ተከትሎ በትናንትናው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉ ተሰምቷል።

ሕጿኗ የተደፈረችው ረቡዕ ሰኔ 14/ 2015 ማታ 11 ሰዓት አካባቢ ሲሆን፤ የሰልፉ መነሻ ሕጻኗን “የመከላከያ ሰራዊት አባል ነው የደፈራት” በሚል ምክንያት መሆኑን አዲስ ማለዳ ከአካባቢው ነዋሪዎችና ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘችው መረጃ ያመለክታል፡፡

ማኅበረሰቡ ሰልፍ ወጣው የሕጻኗን መደፈር ምክንያት አደርጎ ቢሆንም፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ረቡዕ ዕለት ከ11 ሰዓት ጀምሮ ራሱን “ፋኖ” ብሎ በሚጠራው ተጣቂ ኃይል እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።መከላከያ በደላንታ ወረዳ ዙሪያ ጊዜያዊ ካምፕ እንዳለው የጠቆሙት ነዋሪዎቹ፤ ከታጣቂ ኃይሉ ጋር የተኩስ ልውውጥ መደረጉን ተከትሎ በአካባቢው የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት አካባቢውን ለቆ መውጣቱን ጠቁመዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የደላንታ ወረዳ የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ መዝገበ ፈንታው፤ የመከላከያ አባካቱ ረቡዕ ሰኔ 14/2015 አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

የሰላማዊ ሰልፉ ዋና አላማ “በመከላከያ ሰራዊት አባል ተደፍራለች የተባለችውን ሕጻን ፍትህ እንዲሰጣትና የመከላከያ ሰራዊት ከከተማዋ ይውጣ የሙል አቋም የተንጸባረቀበት እንደሆነ መዝገበ አብራርተዋል፡፡

ተድፍራለች የተባለችው የስምንት ዓመት ሕጻን በከተማው ጤና ጣቢያ በሕክምና ላይ መሆኗን የጠቆሙት መዝገበ፤ “በተኩስ ልውውጡ እና በሰላማዊ ሰልፉ የተጎዳ አካል መኖሩን ማረጋጋጥ አልቻልንም” ብለዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here