‹‹ከሕወሓት በስተቀር ሶስቱም የኢሕአዴግ ድርጅቶች የውህደት ሰነዱን አፅድቀውታል››

0
996

‹‹ከሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ(ሕወሓት)በስተቀር ሶስቱም የኢሕአዴግ ድርጅቶች የውህደት ሰነዱን አፅድቀውታል››ሲሉ የግንባሩ ጽሕፈት ቤት የፓርቲዎችና የሲቪክ ጉዳዮች ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ ተናገሩ ሲል አዲስ ዘመን ዘግቧል። የኢህአዴግን የውህደት ጉዞ እዉን ለማድረግ የተከናወነው የጥናት ሰነድ ወደ ተግባር እንዲገባ ከሕወሓት በስተቀር ሦስቱም ማለትም አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ)፣ ኦሮሞ ዴሞክሪሲያዊ ፓርቲ(ኦዴፓ)እና ደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ሰነዱን ማጽደቃቸውን ገልጸዋል። በ11ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ውህደቱን እውን ለማድረግ ጥናት መደረጉን ያስታወሱት ፍቃዱ በየደረጃው ጉዳዩን በተመለከተ ውይይት መደረጉን ተናግረዋል። ምንም እንኳን ሕወሓት ውህደቱን በተመለከተ አቅጣጫ ሲቀመጥ እንደሌሎቹ የኢሕአዴግ አባላት ድርጅቶች በሙሉ ድምጽ ቢያጸድቅም ሰነዱን በተመለከተ ምላሽ አለመስጠቱን ተናግረዋል። ሕወሓት በየኢህአዴግ ዉሰጥ የአመራር ለውጥ ከመደረጉ በፊት ውህደቱ እንዲደረግ ሲወተውት እንደነበር ያስታወሱት ፍቃዱ የሃሳብ ለውጡ የመጣው በቅርቡ ነው ሲሉ ወቀሳቸውን ሰንዝረዋል። አዲስ ማለዳ ከዚህ ቀደም በጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አሕመድ የሚመራው ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ‹‹የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ›› የሚል ውህድ ፓርቲ ለማቋቋም ጫፍ ላይ መድረሳቸውን መዘገቧ ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here