ወደ ሱዳን ሊሻገር የነበረ አደንዛዥ እፅ፣ የዝሆን ጥርስ፣ ደረቅ ጫት እና ነዳጅ መያዙ ተገለጸ

0
559

አርብ ሰኔ 30 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ)

ወደ ሱዳን ሊሻገር የነበረ አደንዛዥ ዕፅ፣ የዝሆን ጥርስ፣ ደረቅ ጫት እና ነዳጅ በሑመራ ከተማ፣ ዲማ፣ ባዕከር እና ራዊያን ኬላ መያዙ ተገለጸ፡፡

መነሻውን ሻሸመኔ ያደረገ እና ወደ ሱዳን ሊሻገር የነበረ 22 ማዳበሪያ ሐሽሽ እንዲሁም መነሻውን አዲስ አበባ ያደረገ በቁጥር 25 ፍሬ ኮኬይን አደንዛዥ ዕፅ መያዙን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም ባለ 25 እና 20 ሊትር 42 ጀሪካን ነዳጅ ፣ 19 ካርቶን ደረቅ ጫት እንዲሁም አራት የዝሆን ጥርስ መያዙ ተገልጿል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here