ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 5/2012

0
1121

1-በአማራና ኦሮሞ ሕዝቦች ስም ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ሰባት ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ።ፓርቲዎቹም የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( አዴፓ) የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ኦዲፒ) የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ( ኦነግ)፣ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ( ኦፌኮ) ፣ የኦሮሚያ ብሄራዊ ፓርቲ (ኦብፓ) እና የአማራ ማህበራዊ ራዕይ ግንባር ናቸው።በኹለቱ ክልሎች እና ዩኒቨርሲቲዎች እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች እንዲቆሙ የድርሻቸውን በመወጣት በአማራና በኦሮሞ ሕዝቦች አንድነት ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)
…………………………………………………………….
2-የዓለም የጤና ድርጅት “እጅግ በጣም ውድ” የሆነውን የኢንሱሊን ዋጋ ዝቅ ለማድረግ የሚያስችል መርሃ ግብር አስተዋውቋል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የተለያዩ የኢንሱሊን ዓይነቶችን እንዲያመርቱ ይፈልጋል። መድሀኒቱንም ራሱ ለመሞከር ፍላጎት እንዳለው ነው ድርጅቱ ያስታወቀው።ኢንሱሊን በፈረንጆቹ በ1923 ከተገኘ ወዲህ በአሜሪካ የመድሃኒቱ ዋጋ ከ1 ዶላር ወደ 300 ዶላር ማሻቀቡ ተገልጿል።(ኢቢሲ)
…………………………………………………………….
3-የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከአንድ ዓመት በፊት በባቡር ምህንድስና ሙያ በማስተርስ ደግሪ ያስመረቀወን የአንድ ተማሪ ድግሪ ሰረዘ።የማስተርስ ዲግሪዉ የተነጠቀው ተማሪም ለመመረቂያ ያቀረበው ፅሁፍ 76 በመቶው ከሌሎች የመመሪቂያ ፅሁፍ ጋር ተመሳስሎ መገኘቱን ተናግሯል። ዩኒቨርሲቲው የጥናታዊ ፅሁፎችን የአእምሮአዊ ንብረት ባለቤትነት የሚያረጋግጥበትን ቴክኖሎጂ ያስገጠመ ሲሆን በዚሁ ቴክኖሎጂም የተማሪዎችን ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ ምርመራ ያደርጋል። 67 በመቶው ደግሞ ከአንድ የመመሪቂያ ፅሁፍ ጋር አንድ አይነት ሆኖ በመገኘቱ ማጭበርበሩን ሴኔቱ አረጋግጦ የማስተርስ ዲግሪዉ እንዲነጠቅ መወሰኑን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)
…………………………………………………………….
4-የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች የአለባበስ ስርዐት መመርያ ህዳር 5/2012 ይፋ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን አስታወቁ።ይህ የአለባበስ ስርዐት የጤና ተቋማትን የአሰራር ሂደት ለመቀየር የተቀረፀው ያገባኛል የሪፎርም ስራ አንድ አካል ነው ያሉ ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ የጤና ባለሙያዎች የአለባበስ ስርዐት ማዘጋጀት በህመምተኛውና በጤና ባለሙያ መሀል ያለውን እምነትና ግልፅነት የሚያጠናክር እና የጤና ባለሙያውንና ተገልጋዩን ከኢንፌክሽን ለመከላከል የሚረዳ መሆኑም ተጠቁሟል።(ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
…………………………………………………………….
5-በተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ ወቅት ተማሪዎችን የትራንስፖርት እጥረት እና እንግልት እንዳይገጥማቸው አንስቶት የነበረውን የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች የኪሎ ሜትር ገደብ ወደ ነበረበት መመለሱን የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል።(አዲሰ ማለዳ)
…………………………………………………………….
6-የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በሕገወጥ መሬት ወራሪዎች ምክንያት ዘመናዊ ቄራ መገንባት አለመቻሉን አስታወቀ።2012 ግንባታዉን ለማጠናቀቅ ዕቅድ የተያዘለትና ለ1ሺ 500 ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ዘመናዊ የቄራ እስካሁን ግንታባው አልተጀመረም። ቄራው ይገነባበታል ተብሎ የተለየው መሬት ላይ ከ500 በላይ ሰዎች በሕገወጥ መንገድ በመስፈራቸው ምክንያትለግንባታው ከፈረንሳይ ልማት ድርጅት በአነስተኛ ወለድ 70 ሚሊየን ዩሮ በብድር ግማሽ ሚሊዮኑ ደግሞ በእርዳታ ቢገኝም የመሬት ጉዳዩ መፍትሄ ባለማግኘቱ ገንዘቡን ማስለቀቅ እንዳልተቻለም የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ንብረቱ በቃ ተናግረዋል።(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)
…………………………………………………………….
7-አንድ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ተማሪ ህዳር 4/2012 ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ ከዩኒቨርስቲው ውጪ ቀበሌ 09 ልዩ ስሙ ባሶ ትምህርት ቤት በሚባለው አከባቢ ጉዳት ደርሶበት ደብረ ብርሐን ሆስፒታል ገብቶ ሕክምና ቢደረግለትም ሕይወቱ ማለፉን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታዉቋል። (አዲስ ማለዳ)
…………………………………………………………….
8-በኢትዮጵያ በመንግስት እና በግል አጋርነት ጥምረት የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተግባራዊ ሊደረግ ነው።ይህን እውን ማድረግ የሚያስችል ዝርዝር ጥናት እንዲደረግም በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ የተቋቋመው የመንግስትና የግል አጋርነት ቦርድ ውሳኔ አሳልፏል።በቦርዱ ውሳኔ መሰረትም ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዳማ – አዋሽ – ሚኤሶ – ድሬዳዋ የፍጥነት መንገድን በጥምረቱ ለመገንባት የአዋጭነት ጥናት እንዲካሄድ ወስኗል።(ዋልታ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here