የቻይና ኩባንያ ግዙፍ የመኖሪያ መንደር ሊገነባ ነው

0
572

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጎተራ አካባቢ ግዙፍ የመኖሪያ መንደር ለመገንባት ሲሲሲሲ ተብሎ ከሚጠራው የቻይና ኩባንያ ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቀ። የመኖሪያ ግንባታው የሚካሔደው ከዚህ ቀደም ሙገር ሲሚንቶ የነበረበት ቦታን ጨምሮ 27 ሄክታር መሬት ላይ ሲሆን ፕሮጀክቱን ወደ ተግባር ለመቀየር የመሬት ዝግጅት መጀመሩን አስተዳደሩ ይፋ አድርጓል።

ከሦስት ሳምንታት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት፤ ባለፈው ሳምንት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ የተጎበኘ ሲሆን ያለበትንም ደረጃ ተመልከተዋል።

አስተዳደሩ ግንባታው መቼ እንደሚጀመር በግልፅ ይፋ ባያደርግም በ2012 በጀት ዓመት ሊጀመር ዕቅድ እንደተያዘ መረጃዎች ያሳያሉ። ባለፈው በጀት ዓመት፤ በለገሃር አካባቢ ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት በዱባይ ኩባንያ የሚገነባ ግዙፍ የመኖሪያ መንደር ግንባታ በይፋ መጀመሩ ይታወሳል። በአሁኑ ወቅትም ግንባታው ለመጀመር የመሬት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቤት ፈላጊዎች ያሉ ሲሆን መንግሥት ባለፉት ዐስርት ዓመታት ይህንን ፍላጎት ለሟሟላት ቃል ቢገባም ገንብቶ ማስረከብ የቻለው 200 ሺሕ እንኳን አይሆንም። ይህንንም በመረዳት ከግሉ ዘርፍ ጋር በአጋርነት ቤቶችን ለመገንባት መንግሥት እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወሳል።

ቅጽ 2 ቁጥር 54 ህዳር 6 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here