ኤምፔሳ (M-PESA) አገልግሎት ጀመረ

0
406

ረቡዕ ነሐሴ 10 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት የሆነው ኤምፔሳ (M-PESA) ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአገልግሎት ፍቃድ ካገኘ ከሦስት ወራት በኋላ ከዛሬ ነሐሴ 10/2015 ጀምሮ አገልግሎት መጀመሩን አስታውቋል።

ባለፉት ሦስት ወራት አስፈላጊ የሲስተም ፍተሻዎችን እና የቴክኒክ ዝግጅቶችን ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ከባንኮች ጋር የሚያስፈልጉትን የአጋርነት ስምምነቶች በመፈራረም እንዲሁም ወኪሎችንም በመመልመል እና በማሰልጠን ወደ ሥራ መግባቱ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት ኹሉም የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደንበኞች የኤምፔሳ አገልግሎትን ለማግኘት እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን፤ የአንድሮይድ (Android) እና የአይኦኤስ (IOS) ስልክ ተጠቃሚዎች በሳፋሪኮም መስመራቸው *733# ላይ በመደወል የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ተብሏል።

የኤምፔሳ መተግበሪያ በ5 ቋንቋዎች የተዘጋጀ እና የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች ከፕሌይስቶር በማውረድ መጠቀም የሚችሉት ሲሆን፤ የአይኦኤስ (IOS) ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በቀጣዩ ሳምንታት በአፕስቶር እንደሚያገኙም ተገልጿል።

የሳፋሪኮም ደንበኞች ኤምፔሳን በመጠቀም በአገር ውስጥ ገንዘብ መላክ፣ ከአገር ውስጥና ውጪ ገንዘብ መቀበል፣ ክፍያዎችን መክፈል፣ የአየር ሰዓት መግዛት፣ ወደ ባንክ ሒሳቦቻቸው ገንዘብ ማስገባት ከባንክ ሂሳባቸው ገንዘብ ወደ ኤምፔሳ መላክ መላክ እንደሚችሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here