የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔን ውጤት ነገ ኅዳር 13/2012 ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ

0
690

በመላው ሲዳማ ዞን በ1692 የምርጫ ጣቢያዎች የተካሔደውን የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔን ውጤት በተመለከተ ነገ ኅዳር 13/2012 ይፋ እንደሚደረግ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ቦርዱ እንደገለፀው በድምጽ መስጫው ማምሻ ላይ ቆጠራው ተጠናቆ የሕዝበ ውሳኔው ውጤት በምርጫ ጣቢያዎች ይፋ ተደርገዋል። በትናንትናው ዕለት ኅዳር 11/2012 የኹሉም ምርጫ ጣቢያዎች ውጤት ተጠናቀው ወደ 15ቱም ማስተባበሪያዎች እንደገቡም ቦርዱ አስታውቋል። በዚህ መሰረት ኹሉም የሚመለከታቸው አካላት ውጤቱን በትዕግስት እንዲጠባበቁ ቦርዱ አሳስቧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here