አርብ ነሐሴ 26 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በመቅደላ አምባ በወቅቱ ከተዘረፉ ቅርሶች መካከል የቅዱስ ሚካኤል መስቀል እንደሆነና፤ በወቅቱ ከመቅደላ የተወሰደ መሆኑን በእንግሊዘኛ የተከተበበትን ቅርስ ሩት ኢማኑኤል ዛሬ ነሐሴ 26/2015 ለኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስረክበዋል።
በርክክቡ ወቅት ክብርት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣ ዶ/ር አሉላ ፓንክረስ፣ ረ/ፕ አበባው አያሌው፣ ኩመራ ዋቅጅራ በተገኙበት ርክክብ መደረጉን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።



