ማክሰኞ መስከረም 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በከተማዋ በሞተር ብስክሌተኞች፣ በባለ አራት እግር እና ባለሦስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥሎት የነበረውን ክልከላ ከዛሬ ማክሰኞ መስከረም 29/2016 ጀምሮ ማንሳቱን አስታውቋል።
ቢሮው ፍቃዱ የባጃጅ አሽከርካሪዎች በቢሮው እውቅና ተሰጥቷቸው በማህበር ተደራጅተው መስመርና ታፔላ ያላቸው እንዲሁም፤ የሞተር ሳይክሎች በአዋጁ መሰረት ሰሌዳ ወስደው፣ ሕጋዊ መንቀሻቀሻ ፍቃድና ጂፒኤስ(GPS) ያስገጠሙትን ብቻ የሚመለከት መሆኑን ገልጿል።
ከትራንስፖርት ቢሮው ሕጋዊ እውቅና ውጪ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ ቢሮው ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አሳስቧል።



