የጤና መታወክ ያጋጠማቸው ታዳጊ ተማሪዎች ሕክምና ተደርጎላቸው ለቤተሰቦቻቸው ተመልሰዋል

0
781

በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ፍሬህይወት ቁጥር አንድ ትምህርት ቤት ዛሬ ኅዳር 17/2012 ጠዋት ላይ 25 ተማሪዎች እና 5 አስተማሪዎች ላይ በተፈጠረው የጤና ዕክል ምክንያት ወደ ጥቁር አንበሳ እና ዘውዲቱ ሆስፒታሎች የተወሰዱ ተማሪዎች ከኹለት ተማሪዎች በስተቀር ቀሪዎቹ ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሳቸውን የትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር ፍርህይወት አዳል ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል። የ5እና የ7ኛ ክፍል የሚማሩ በተማሪዎቹ እና በአስተማሪዎቹ ላይ የማሳል ፣ማስመለስ፣ብርድብርድ የማለት እንዲሁም እራሳቸውን የመሳት ምልክት መታየቱን ገልጸዋል።በትምህርት ቤቱ በሚሰጠው የምግብ አገልግሎት 700 ተማሪዎች የሚመገቡ ሲሆን ነገር ግን 25 ተማሪዎች ብቻ መታመማቸው ታውቋል። የጤና ዕክል ካጋጠማቸው አንዱ የሆነው ተማሪ ፉአድ ለአዲስ ማለዳ እንደገለፀው ጠዋት ለቁርስ የተመገቡት ዳቦ በማር ሲሆን ከተመገቡ በኋላ ሕመም እንደጀመራቸው አስታውቋል በቦታው የተገኙት አዲስ አበባ ጤና ቢሮ ባለሞያዎች ተማሪዎች ጠዋት የተመገቡት ምግብ ለምርመራ ናሙና መውሰዳቸውን የገለፁ ሲሆን ምርመራው እንደተጠናቀቀ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። በአሁን ሰዓት ከኹለት ተማሪዎች ውጭ ሁሉም ተማሪዎች በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ በመገኘታቸው ለቤተሰቦቻቸው መመለሳቸውን ፍርህይወት አዳል ገልጸዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here