ሸገር ዳቦ የምርት ስርጭቱን ከፊታችን አርብ ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር ተገለጸ

0
173

ማክሰኞ ጥቅምት 20 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረው ሸገር ዳቦ የምርት ስርጭት ከፊታችን ከአርብ ጥቅምት 23/2016 ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የንግድ እና ግብይት ዘርፍ ም/ ቢሮ ኃላፊ መስፍን አሰፋ፤ የሸገር ዳቦ የምርት ስርጭት አርብ ዳግም እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሰረት የአንድ ዳቦ ዋጋ 5፡00 ብር መሆኑን የገለጹት ም/ቢሮ ኃላፊው፤ በአቅርቦት ረገድም በኹሉም አካባቢ ተደራሽ ለማድረግ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡

በቀን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዳቦ በላይ የሚያመርተው ድርጅቱ በተለይ ከስንዴ አቅርቦትና ግዢ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ ክፍተት ምርቱ በመዲናዋ ማሰራጨት ካቆመ ከስድስት ወራት በላይ ማስቆጠሩ ይታወቃል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here