ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ አንድ ሺሕ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶችን ልትገነባ ነው ተባለ

0
287

ሐሙስ ጥቅምት 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮጵያ በ23 ከተሞች የውሃ አያያዝና አቅርቦትን ለማሻሻል የ523 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት መጀመሯ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም ፕሮጀክት በመላ አገሪቱ 1 ሺሕ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች መገንባትን እንደሚያካትት ተነግሯል፡፡

ለዚሁ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያም የዓለም ባንክ የ460 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ቀሪውን 63 ሚሊየን ዶላር ደግሞ በሌሎች ለጋሽ ተቋማት ይሸፈናል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባትን የመቀሌ ከተማ የሚያካትት መሆኑን አዲስ ማለዳ ከአለም አቀፍ ኮንስትራክሽን ሪቪዉ ያገኘችዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ በከተማዋ የውሃ መሰረተ ልማቶችን ለማዳረስ እንዲሁም የኤሌክትሪክ ፓምፖች ለመግዛት 1 ሚሊየን ዶላር ወጪ ማድረጓም ተነግሯል፡፡

በፈረንጆቹ 2018 ግሎባል ዋተር ኢንተለጀንስ የተሰኘው ተቋም አደረኩት ባለው ጥናት መሰረት፤ በአገሪቱ ዘመናዊ መጸዳጃ የሚጠቀሙ የከተማ ነዋሪዎች 12 በመቶ ብቻ መሆናቸውን አመላክቷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here