በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ ሲካሔድ የቆየው ስብሰባ ተጠናቀቀ

0
536

በኅዳር 5 እና 6/2012 በአዲስ አበባ በኅዳሴው ግድብ የውሃ ሙሊት እና ውሃ አለቃቀቅ ዙሪያ ምክክር ተደርጎ ዕልባት ላይ ባልተደረሰባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ ሲወያዩ የቆዩት የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የውሃ ሚንስትሮች ስብሰባ ዛሬ ኅዳር 23/2012 ተጠናቋል።

የኢፌዴሪ ውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር  ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) የአባይ ውሃ ለኢትዮጵያ ድህነትን ማጥፊያ እና የህልውና ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፥ የአሁኑንና የወደፊት ትውልድ የመጠቀም መብትን የማይገድብ መሆኑን ተናግረዋል። ሲል ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል።

የሦስቱ አገራት ሚንስትሮች በቴክኒካዊ ጉዳይ ላይ ያካሔዱት ስብሰባ የዓለም ባንክ እና የአሜሪካ መንግሥት ተወካዮች በታዛቢነት የተገኙበት እንደነበርም የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here