ኢትዮጵያ ሳተላይት የምታመጥቅበት ቀን በሦስት ቀናት ተራዘመ

0
1022

ኢትዮጵያ በታሪክ የመጀመሪያዋ የሆነችውን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ወደ ሕዋ ለመላክ በታኅሳስ 7/2012 መርሃ ግብር ተይዞለት የነበረ ቢሆንም በሦስት ቀናት እንዲገፋ መደረጉ ታወቀ። ሳተላይቷ ከቻይና የምርምር ጣቢያ ወደ ሕዋ የምትመጥቅ ሲሆን፤ በከተማው ያለው የአየር ሁኔታ ሳተላይቷን ወደ ሕዋ ለማስወንጨፍ አስቸጋሪ በመሆኑ በሦስ ቀናት ተራዝሞ ታኅሳስ 10/2012 እንዲሆን መደረጉን የኢፌዲሪ የሳይንስና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር አስታውቋል።

ETRSS-1 የተሰኘችው የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ወደ ሕዋ በመጓዝ በርካታ መረጃዎችን ወደ ምድር እንደምትልክ የታመነባት ሲሆን፤ በተለይም ደግሞ ለግብርናው ዘርፍ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚኖረው መረጃ ወደ ምድር እንደምትልክ ታውቋል።

ከሳተላይት ማምጠቁ ጋር ተያይዞም ኢትዮጵያ የሳተላይት መቆጣጠሪያ እና መረጃ መቀበያ ጣቢያ በእንጦጦ ኦብዘረቫቶሪና ምርምር ማዕከል ውስጥ በመገንባት ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ የሳተላይት መረጃ መቀበያ አንቴና ግንባታውም በቅር መጠናቀቁ ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here