ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 24/2012

0
480

1–የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ከ6 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የ299 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው አራት የአስፋልት መንገዶች ሊያስገነባ መሆኑን አስታወቀ።ባለስልጣንኑ ለሚያስገነባቸው መንገዶች ከአሸናፊ ተቋራጭ ጋር ነገ ኅዳር 25/2012የስምምነት ፊርማ ያከናውናል።ግንባታው የሚከናወንባቸው አራቱ መንገዶች የሐሙሲት -እስቴ ፣የፍሰሀገነት -ኮሌ-ሰገን-ገለባኖ ሎት 2 የጩልሴ-ሶያማ፣የጎዴ ቀላፎ-ፌርፌር እና የአደሌ-ግራዋ መሆናቸው ታውቋል።(አብመድ)
…………………………………………………………………………….
2-በኢትዮጵያ የሚገኙ የኃይል ማመንጫ ግድቦች በቂ ውሃ በመያዛቸው ወደ ፈረቃ ስርዓት እንደማይገባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሰታወቀ።ግድቦቹ ካለፉት አመስት አመታት ከነበራቸው አማካይ የውሃ መጠን ያልተናነሰ ውሃ በመያዛቸውና በቂ ውሃ በመኖሩ ዘንድሮ በኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት የፈረቃ ስርዓት እንደማይኖር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙዩኒክሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን ገልጸዋል።(ኢቢሲ)
…………………………………………………………………………….
3- -በፈረንጆቹ በ2025 ያለ እድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛትን በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት አዲስ አገር አቀፍ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጀ። በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ፆታዊ ጥቃት ለማስቆም እንደሚያግዝ ተገልጿል።የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉበኤ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቆም በባለቤትነት መስራት እንደሚገባውም ተጠቁሟል።(ኢቢሲ)
…………………………………………………………………………….
4-የምርትና አገልግሎት የዋጋ ግሽበት ለተከታታይ አራት ወራት ጭማሪ በማሳየት ጥቅምት ወር ላይ 18 ነጥብ 6 በመቶ መድረሱን የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ።የዋጋ ንረቱ በከፍተኛ ደረጃ የጨመረው በተለይ በምግብ ነክ በሆኑ ምርቶች እንደሆነም በኤጀንሲው የስታስቲክስ ጥናቶችና ኢኮኖሚያዊ ቆጠራዎች ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አማረ ለገሰ ተናግረዋል።ይህም ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮ ጥቅምት ወር ላይ ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶችና አገልግሎቶች ዋጋ ግሽበት 13 ነጥብ 4 በመቶ የደረሰ ሲሆን ምግብ ነክ የሆኑ ምርቶች ደግሞ 23 ነጥብ 2 በመቶ መጨመሩን ተናግረዋል። (ኢቢሲ)
…………………………………………………………………………….
5-በአማራ ክልል ደብረ ብርሃን ከተማ እና አካባቢዋ ከ100 ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን የአማራ ኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሸን ገለፀ።በአካባቢው በተገነቡ አራት ሁለገብ የኢንዱስትሪ መንደሮች እስካሁን ለ27 ሺሕ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር መፈጠር እንደተቻለየ የኮርፖሬሽኑ ደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ ቢሮ ኃላፊ ተሾመ ገብረ አምላክ ተናግሯል።በፕላስቲክና ኬሚካል ማምረት ላይ የተሰማሩ 70 የሚደርሱ ፕሮጀክቶች በዘርፍ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸውም ገልጸዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)
…………………………………………………………………………….
6-አዲሱ የደህንነት ቀበቶ መመሪያ ከጥቅምት 18/2012 ጀምሮ ለአሽከርካሪውና ለሁሉም ተሳፋሪዎች የፀና እንደሚሆን ተገለጸ።መመሪያው በመንግስትና በግል ለሰራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች፣ እስከ 150 ኪሎ ሜትር በሚጓዙ ሚኒባሶች እና የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፣ ከ5 እስከ 8 መቀመጫ ያላቸው ተሽከርካሪዎች፣ ረጅም ርቀት የሚጓዙ ልዩ ባሶችና አገር አቋራጭ አውቶብሶች ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል።(ዋልታ)
…………………………………………………………………………….
7–በጅቡቲ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር አብዱልአዚዝ መሐመድ መንግስት ወደ አገር ቤት ለማስገባት ያቀደውን ከፍተኛ መጠን ያለውን የስንዴ ጭነት በተቀላጠፈ አሰራር ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ በጅቡቲ ኮሪደር ከሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ማኅበራት ጋር ውይይት አድርገዋል።ውይይቱ መንግስት ወደ አገር ለሚያስገባው ስንዴ በጅቡቲ ከሚገኙ የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር በቅንጅት በሚተገበርበት ሁኔታ ላይ ለመምከር የታለመ መሆኑን ተገልጿል።(አዲስ ማለዳ)
…………………………………………………………………………….
8-በጅቡቲ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የአፍሪካ የብልጽግና ጉባዔ ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ አፍሪካ አገራት ተሳትፈዋል።ጉባዔው በጅቡቲ ንግድ ምክር ቤት ከፓን አፍሪካ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን የጉባዔው መዘጋጀት በአፍሪካ ለሚመሰረተው ነፃ የንግድ ቀጠና የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።(ኢቢሲ)
…………………………………………………………………………….
9-በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ አመራሮች በመደመር እሳቤ ስልጠና ላልወሰዱ አመራሮች ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበርያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል ተስፈዬ በልጅጌ ለሰልጣኞች ኦረንቴሽን ተሰጥተዋል። የስልጠናው ዋና አላማ በመደመር እሳቤ ላይ አመራሩ ግንዛቤ እንዲያገኝና ግልጽነት እንዲኖረው ያስችላል ተብሏል። (አዲስ ማለዳ)
…………………………………………………………………………….
10-የዳቦ መቀነስና የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ለችግር እየዳረጋቸው መሆኑን የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።በመቀሌ ከተማ ዳቦ በማምረትና በማከፋፈል ስራ የተሰማሩ ነጋዴዎች የዳቦ መጠን በመቀነስና ዋጋ በመጨመራቸው መሆኑን ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል።(ኤዜአ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here