የሰው አልባ በራሪ ቁሶች መተዳደሪያ ደንብ እየተዘጋጀ ነው

0
716

ወደ አገር በሚገቡ እና በሚወጡ ሰው አልባ በራሪ ቁሶች (drone) አጠቃቀም ዙሪያ መተዳደሪያ ደንብ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኢጀንሲው እንዳስታወቀው የድሮን አጠቃቀም ከሌሎች አገራት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ሚባል ቢሆንም ቁሶቹ ለእኩይ ተግባር እንዳይውሉ መተዳደሪያ ደንቡ መዘጋጀት እንዳስፈለገ ታውቋል።

ከዚሁ በተጨማሪም ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ ቁሶች ላይ ኤጀንሲው ተገቢውን ምርመራና ፍተሻ ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር እንደሚያካሂድ ለማወቅ ተችሏል።

በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ሲቪል አቬይሽን ባለሥልጣንና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በቅንጀት እየሰሩ ይገኛል።
ድሮኖች ለኢንጅነሪንግ፣ ለኮንስትራክሽን፣ ለቅድመ-ኮንስትራክሽን ሥራ፣ ለአቬሽን፣ ለባህር ትራንስፖርት፣ ለንግድ፣ ለሪልስቴት፣ ለኢንሹራንስ፣ ለአገልግሎት፣ ለማዕድን፣ ለሜትሮሎጂ፣ ለትምህርት እና ለሌሎች መሰል ተግባራት ይውላሉ።

መመሪያው ተጠናቆ ወደ ትግበራ ሲገባ በአገር ውስጥ በግለሰብ ደረጃም ሆነ ለተቋማት አገልግሎት ስለሚውሉ የድሮን ዓይነቶች እና ድሮኖቹ እንዲንቀሳቀሱ የሚፈቀድላቸው የዓየር ክልል፣ ከመሬት የከፍታ መጠን፣ ክብደት፣ የበረራ ፈቃድና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በመያዝ ተፈፃሚ እንደሚሆን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አሰታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here