ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 25/2012

0
750

1-በያዝነው በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።ከማምረቻው ዘርፍ 779 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን ከማዕድን ዘርፍ 261 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም ቀሪውን ደግሞ ከተለያዩ ዘርፎች ለማግኘት መታቀዱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)
…………………………………………………………………………………………….
2–በጎንደር ከተማና በዙሪያ የገጠር ቀበሌዎች በቅርቡ ተከስቶ በነበረው ግጭት የተጠረጠሩ 156 ግለሰቦች ለሕግ መቅረባቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ። በግጭቱ ምክንያት የ43 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በዘጠኝ ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።(ኢዜአ)
…………………………………………………………………………………………….
3-ባለፉት 7 ወራት በውጭ ከሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን 4 ሚሊዮን ዶላር መሰብሰቡን የኢትዮጵያ የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ አስታወቀ።በፈረንጆቹ 2019 ከገባ ወዲህ ባለፉት 7 ወራት ውስጥ ብቻ 4 ሚሊዮን ዶላር መሰብሰቡን የኢትዮጵያ የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ስራ አስኪያጅ ፍቅሬ ዘውዴ ገልጸዋል።ትረስት ፈንዱ በተቋቋመበት አመት በ2018 1ነጥብ 2 ሚለዮን ዶላር ብቻ ነበር መሰብሰብ የቻለ ሲሆን በአጠቃላይ ትረስት ፈንዱ እውን ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በአሁኑ ሰዓት 26 ሺሕ ሰው ባደረገው አስተዋፅኦ በአጠቃላይ 5 ሚሊዮን 262 ሺሕ ዶላር ማሰባሰቡን ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል።(ኢቢሲ)
…………………………………………………………………………………………….
4-በአዲስ አበባ አራት ክፍለ ከተሞች በ132 ሔክታር መሬት ላይ የመናፈሻ ፓርኮች ሊገነቡ መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ኮሚሽነር ዓለም አሰፋ አስታውቀዋል። በከተማዋ የመናፈሻ ፓርኮች ለኅብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት የተሻለ ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን የሚገነቡት የመናፈሻ ፓርኮች በመንግስት እና በግል አልሚዎች በትብብር የሚለሙ ሲሆን ለበርካታ ሴቶች እና ወጣቶች የስራ እድል እንደሚፈጥሩ ኮሚሽነሯ አስረድተዋል።(ኢዜአ)
…………………………………………………………………………………………….
5–በጎንደር ዩንቨርሲቲ ከ3 ሺሕ በላይ ተማሪዎች የተመዘገቡበት የጎንደር ቤተሰብ ፕሮጀክት የፊታቸን ቅዳሜ ኅዳር 27/2012 በይፋ እንደሚጀመር የጎንደር ዩንቨርሲቲ አስታወቀ።አዲስ ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸዉ እና ከአካባቢያቸዉ ተለይተዉ ዩንቨርሲቲን ሲቀላቀሉ የቤተሰብነት ስሜት እንዲሰማቸዉ በሚል የጎንደር ቤተሰብ ፕሮጀክት እንደተቀረፀ ዩንቨረሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሥራት አፀደወይን ተናግረዋል።(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)
…………………………………………………………………………………………….
6–ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ከፈረንሳይዋ ሊዩን ከተማ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ኬሚልፊልድ ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ ።ስምምነቱ በአዲስ አበባ እና በሊዬን ከተማ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን በተለያዩ መስኮችም በጋራ ለመስራት የሚያስችል ሲሆን የሸገር ፕሮጀክትን ጨምሮ ሌሎች የአረንጓዳ ልማት ስራዎች ላይ የቴክኒክ እና የገንዝብ ድጋፍ ማድርግ በስምምነቱ ከተካተቱ ጉዳዩች መካከል አንዱ ታውቋል።(ኢቢሲ)
…………………………………………………………………………………………….
7-የብልጽግና ፓርቲ የዕውቅና ምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትላንት ኅዳር 24/2012 ጥያቄ አቅርቧል።በቅርቡ ውህደት የፈጸሙት የኢህአዴግ እህትና አጋር ፓርቲዎች ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተሰጥቶ የነበረውን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሰርዝ ጠይቋል። በውህደት የተመሰረተውን የብልጽግና ፓርቲን እንዲመዘገብና ዕውቅና እንዲያገኝ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማስረከቡን ገልጿል።(አዲስ ማለዳ)
…………………………………………………………………………………………….
8-የኦሮሚያ ልማት ማህበር ያስገነባውን ሁለተኛ የአዳሪ ትምህርት ቤት በቢሾፍቱ ከተማ አስመርቋል።በትምህርት ቤቱ ምረቃ ስነስርዓት ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የልማት ማህበሩ ቦርድ ሰብሳቢ አባዱላ ገመዳና የተለያዩ አመራሮች ተገኝተዋል።በአዳሪ ትምህርት ቤቱ 270 የሚደርሱ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተገልጿል።(ዋልታ)
…………………………………………………………………………………………….
9-የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ( Lowlands Livelihood Resilience project ) በ451 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይፋ ተደረገ።ፕሮጀክቱ በሱማሌ ፣ በአፋር ፣ በኦሮሚያ ፣ በቤንሻንጉል ፣ በጋምቤላና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች የሚገኙ አርብቶና ከፊል አርሶ አደሮችን የሚሸፍን ሲሆን አጠቃላይ 100 ወረዳዎችን ያካትታል ሲሆን ይህ ፕሮጀክቱ ለ6 ዓመታት የሚቆይ ሲሆን 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሕዝብ ወይም ከ500 ሺሕ በላይ አባዉራዎች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል ።(ኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here